የፕሬዚዳንት ባይደን የአዉሮጳ ጉብኝት
ዓርብ፣ ሰኔ 4 2013ማስታወቂያ
የዩናትድ ስቴትስን የፕሬዚዳንትነት ስልጣን ከያዙ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አዉሮጳ የመጡት ጆባ ይደን ኮርንዋል በተባለዉ የብሪታንያ የባህር ዳርቻ በሚካሄደዉ ቡድን 7 በመባል የሚታወቁት ባለጸጋዎቹ ሃገራት ጉባዔ ለመካፈል እንጊሊዝ ከገቡ ሁለተኛ ቀናቸዉን ይዘዋል። ፕሬዚዳንት ባይደን ዛሬ በጀመረዉ የቡድን ሰባት ጉባኤ ከተካፈሉ በኋላ የፊታችን ሰኞ የአዉሮጳ ኅብረት መቀመጫ በሆነዉ በብራስልሱ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ሃገሮች ማለትም በ «ኔቶ» የመሪዎች ስብሰባ ላይ እንደሚካፈሉ ይጠበቃል። የፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን የአዉሮጳ ጉብኝት እና አንደምታዉን በተመለከተ፤ የብረስልሱ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ