የፕሬስ ይዞታ በኢራን
ረቡዕ፣ ሰኔ 10 2001ማስታወቂያ
ለሶስት አስርት ዓመታት በሀይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ምክንያቶች የፕሬስ ቅድመ ምርመራ በሚካሄድባት በኢራን የአንዳንድ ዓለም ዓቀፍ ነፃ መገናኛ ብዙሀን ስርጭቶች እንደታገዱ ነው ። ከነዚህም ውስጥ ዶይቼቬለ በሀገሪቱ ቋንቋ በፋርስኛ ከቦን የሚያስተልፈው የራድዮ ስርጭት ይገኝበታል ። በኢራን ኢንተርኔትም የታገደ ቢሆንም በአሁኑ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ኢራናውያን በተለያዩ ዘዴዎች በኢንተርኔት ድረ ገፆችና ንዑሳን ድረገፆች ሀሳባቸውን ሲገልፁ እና መልዕክቶቻቸውንም ሲያስተላልፉ ከርመዋል ። ይህ በእጅጉ ያሰጋው መንግስት ፣ በሀገሪቱ ውጥረት ያሰፍናሉ ያላቸው መረጃዎች ከየድረ ገፆች ላይ እንዲነሱ አስጠንቅቋል ። በኢራን የፕሬስ ይዞታ ላይ በማተኮር የዶይቼቬለው ማትያስ ፎን ሀይም ያቀረበውን ዘገባ ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።
ሂሩት መለሰ/አርያም ተክሌ