1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፕረስ ነፃነትና የሐሰት «ዜና»

ዓርብ፣ ሚያዝያ 25 2011

ዕለቱን ምክንያት በማድረግ ከትናንት በስትያ አዲስ አበባ ዉስጥ የተጀመረዉ ዓለም አቀፍ ስብሰባና የሐሳብ ልዉዉጥም ዛሬም ቀጥሎ ነዉ የዋለዉ።ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀችዉ ስብሰባና ዉይይት ላይ የዶቸ ቬለንና የቢቢሲን ጨምሮ የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ተጠሪዎች፣ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎች ተካፍለዋል።

https://p.dw.com/p/3HtBP
Äthiopien Internationaler Tag der Pressefreiheit in Addis Abeba
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

የፕረስ ነፃነት ቀን በአዲስ አበባ

ዓለም አቀፍ የፕረስ ነፃነት ቀን ዛሬ በመላዉ ዓለም በተለያዩ ዝግጅቶች፣ ሥብሰባዎችና ጉብኝቶች ተከብሮ ዉሏል። ዕለቱን ምክንያት በማድረግ ከትናንት በስትያ አዲስ አበባ ዉስጥ የተጀመረዉ ዓለም አቀፍ ስብሰባና የሐሳብ ልዉዉጥም ዛሬም ቀጥሎ ነዉ የዋለዉ።ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀችዉ ስብሰባና ዉይይት ላይ የዶቸ ቬለንና የቢቢሲን ጨምሮ የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ተጠሪዎች፣ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎች ተካፍለዋል።የአዲስ አበባዉ ዉይይት የሐሰት ዜናና መረጃ ስርጭት በፕረስ ነፃነትና በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ላይ ለሚኖረዉ አደጋ ልዩ ትኩረት የሰጠ ነዉ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ