የፔጊዳ ሰልፈኞች እና የጀርመን ገፅታ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 14 2007ማስታወቂያ
የሰልፈኛው ቁጥር ከባለፈው ሳንምት በ2500 ጨምሮ17 500 ደርሷል። ራሳቸውን የቀኝ ፅንፈኞች ብለው ባይጠሩም፤ ለበርካታ ታዛቢዎች ልዩነቱ እንብዛም ግልፅ አልሆነም። በተለያዩ የጀርመን ከተሞች ሰሞኑን በፔጊዳ ስር አደባባይ የሚወጡት ሰዎች በግልፅ የሚናገሩት፤ ወደ ጀርመን የውጭ ሀገር ሰዎች እንዲመጡ እንደማይፈልጉ፤ የእስልምና እምነት ጨርሶ ቦታ እንደሌለው እና ፤ ነፃነት የሚሰማቸው፤ ጀርመን የጀርመናውያን ብቻ ሆና ስትቆይ እንደሆነ ይናገራሉ።
የፔጊዳ ሰልፈኛ አደባባይ የወጣበት ከተማ ፤ ድሬስድን ናት። እንደሚታወቀው ድሬስድን የውጭ ሀገር ዜጋው ቁጥር ከመቶ 4,7 ነው። የድሬስድን ከተማ የምትገኝበት የዛክስን ግዛት እንኳን ከአንድከመቶ ያነሰ የእስልምና ተከተማይ የሚኖርባት የጀርመን ግዛት ነች። ታድያ የህብረተሰቡ ተቃውሞ ከምን የመነጨ ነው?
በርካታ የቀኝ ፅንፈኞች ተቀላቅለውት ይሆናል የሚባለው የፔጊዳ ህብረት በአጭር ጊዜ ውስጥ በውጭ ዜጎች ላይ ጥላቻን የሚያንፀባርቁ ጀርመናውያንን ለማነሳሳት ችሏል። በጀርመን ምናልባት በይፋ ከሚገመተው በላይ ናዚዎች ይኖራሉ ማለት ነው? የፖለቲከኞቹስ አቋም ምን ይመስላል። የፔጊዳን እንቅስቃሴ ከበርሊን የተከታተለው ይልማ ኃይለ ሚካኤል ለጥያቄዎቹ ምላሽ ሰጥቶናል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ልደት አበበ
ሸዋዬ ለገሠ