የፓርቲዎች የክርክር መድረክና የሰማያዊ ፓርቲ ስሞታ
ዓርብ፣ መጋቢት 18 2007ማስታወቂያ
ይህ የተደረገዉም በመጭዉ እሁድ አዲስ አበባን ጨምሮ በ 15 የተለያዩ ከተሞች ለተጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ ሆን ተብሎ ለመጉዳት ነዉ ሲሉ፤ የፓርቲዉ ሊቀመንበር ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት ለዶይቼ ቬለ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲግ ኮርፖሬሽን በበኩሉ የክርክር መድረኮቹ በእጣ መደልደላቸዉን፤ ሰማያዊ ፓርቲ ግን በሰብዓዊ መብቶችና ዲሞክራሲ ላይ በተካሄደዉ ዉይይት አለምደባዉ መሳተፍ አለብኝ ብሎ ከሌላ ፓርቲ ጋር በመቀየሩ፤ ዛሬ ሊሳተፍ አለመቻሉን ገልፆአል። ይህንንም ከሰማያዊ ሰልፍ ጋር አያይዞ ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀምም ተገቢ አይደለም ሲሉ የድርጅቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ተሻለ በቀለ መልስ ሰጥተዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ