የፎቶ ትርዒት፤ የመንደር እና የከተማ ኑሮ በአፍሪቃ
የህዝብ ቁጥር መጨመር ፣ የሚስፋፋው ከተማ ብዛት፣ የሚካሄደው አብዮት - በአጠቃላይ በአፍሪቃ የሚታየው ለውጥ የአፍሪቃ ፎቶ አንሺዎችንም ትኩረት የሳበ ጉዳይ ነው።
ኪነ ጥበብ በተለያየ ገጹ
የህዝብ ቁጥር መጨመር ፣ የሚስፋፋው ከተማ ብዛት፣ የሚካሄደው አብዮት - በአጠቃላይ በአፍሪቃ የሚታየው ለውጥ የአፍሪቃ ፎቶ አንሺዎችንም ትኩረት የሳበ ጉዳይ ነው። የአፍሪቃ ከተሞች ህይወት የዚህ ዓመቱ « የሌጎስ የፎቶ ትርዒት» ርዕስ ሆኖ ነው የከረመው። ለናይጄሪያው ፎቶ አንሺ ኬሊቺ አማዲ-ኦቢ አርቲስት ኬዚያ ጆንስ ትርምስምስ ባለበት የሌጎስ ከተማ ከካሜራው ፊት ቆሞለታል።
በማደግ ላይ ያሉ ትላልቅ ከተሞችና የኪነጥበብ ሰዎች
ከ50 የሚበልጡ ፎቶ አንሺዎች እስከ ህዳር አጋማሽ 2013 ድረስ ሌጎስ ውስጥ በአፍሪቃ ስለሚስተዋለው እድገት አሳይተዋል። « የሌጎስ የፎቶ ትርዒት» በናይጀሪያ የሚቀርብ ብቸኛው ዓለም ዓቀፋዊ ትርዒት ነው። በዚህ አጋጣሚም በዓለም ዙሪያ ያሉ ፎቶ አንሺዎች ተሳትፈዋል።
የደሀው ሰፈር ታዳሚ ፎቶ አንሺዎች
አፍሮ ሱላይማን በ«ሌጎስ የፎቶ ትርዒት» ላይ ሲሳተፍ የመጀመሪያ ጊዜው ነው። ማኮኮ ከምትባል በሌጎስ የምትገኝ መንደር ነው የመጣው። ፎቶ አንሽ መሆን የሁልጊዜ ምኞቱ ነበር። «ባለፈው አመት ወንድሜ አንድ የፎቶ አውደ ጥናት እንዳለ ነግሮኝ ነበር። » ይላል። ሱላይማን ከሌሎች 30 ተካፋዮች ጋር በመሆን ነው አውደ ጥናቱን የተካፈለው። በመጨረሻም እሱና ሌላ አንድ ፎቶ አንሺ ብቻ ከግማሽ ዓመት በኋላ ተመራቂ ለመሆን በቁ።
"ሁሌ ህይወትን የመወጣት ትግል ነው"
በሱላይማን ስራዎች የማኮኮ ነዋሪዎች የዕለት ከዕለት ኑሮ ይንጸባረቃል። በተለይ በአንድ ትንሽ መንደር እንዴት 100 ሺ የሚሆኑ ሰዎች ተጣበው እንደሚኖሩ ያሳያል። በዛም አነሰ ሰዎች ህይወትን ለመወጣት በቂ ገንዘብ ለማግኘት እንደሚታገሉ ያሳያል። » ይላል ሱላይማን። ይህ ሌሎችን ብቻ ሳይሆን እሱንም ይመለከታል። በፎቶ አንሺነት እሱም እስካሁን ራሱን ማስተዳደር አልቻለም።
ለጎረቤት ቅርብ ሲኮን
ሱላይማን ከድሆች ሰፈር መምጣቱን በበጎ ይመለከተዋል። ሰዎቹን ሲያነሳ ጎረቤቶቹ እንጂ የማያውቃቸው ሰዎች አይደሉም። አንዳንዶቹ ጥንቁቅ ናቸው። ያኔ ሌሎች ስለእኛ አኗኗር ቢገነዘቡ ጥሩ ነው ስል አብራራላቸዋለሁ። ያኔ እነሱም ይገባቸዋል።
ከጦርነት እና ግጭት ርቆ
ድህነትን ከሚያንፀባርቁት ፎቶዎች በተቃራኒ የፓትሪክ ዊሎክ ፎቶዎች ቀርበዋል። ፈረንሳዊው ፎቶ አንሽ በዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ ለበርካታ ወራት ኖሯል። በዚህም ወቅት የታዘበው የመንደሩ ነዋሪዎች ምን ያህል በተረጋጋ እና በሰላም እንደሚኖሩ ነው። ይህን የታዘበውን በምስዕ አቅርቧል። « አብዛኛውን ጊዜ በኮንጎ ስላለው ጦርነት ብቻ ነው የምንሰማው» ሲል ያብራራል።
በአጥናፋዊው ትስስር የተነሳ ፕላስቲኮች መንደር ገብተዋል
ዊሎክ ህፃን እያለ ኮንጎ ውስጥ ኖሯል። ፈረንሳዊው ካነሳቸው ፎቶዎች መካከል በአጥናፋዊው ትስስር አማካይነት እልም ያለ ገጠር ውስጥ የፕላስቲክ ወንበሮች ተደርድረው ያሳያል። ይህ ዊሎክ በመገረም የሚያየው ለውጥ ነው። « በኔ አመለካከት ባህላዊ የእንጨት ወንበሮቹ አመቺ፣ ቋሚ እና ጠንካራ ናቸው።»
የተለያየ የኑሮ ገፅታ በሴኔጋል
ፎቶ አንሽ ሞሀመድ ሙስተፋ ሶው የሀገሩ ሴኔጋል የዕለት ከለት ኑሮውን ነው መነጋገሪያ ያደረገው። ለነገሩ ሶው የልብስ ቅድ ነዳፊ( ዲዛይነር) ነው። በትርፍ ጊዜው ብቻ ነው ፎቶ የሚያነሳው። « የእኔ አላማ በአጠቃላይ በዳካር ኑሮ ምን እንደሚመስል ማሳየት ነበር።
ብዙ ነገር ከማዕቀፉ ያለፈ ነው
ፎቶ አንሺው በተለይ የምዕራብ አገሮችን ይወቅሳል። የሚያተኩሩት በአፍሪቃ ያሉ ሁሉም የሚያነሳቸው ጉዳዮች ላይ ነው ይላል። ታድያ የሞሪታንያ በረሃ ውስጥ አንድ ያረጀ ቲሌቪዥን ቀፎ ሲያገኝ አንድ ሀሳብ መጣለት ይህም « ፎቶዎች ካለው የከተማ ህይወት ቀንጭቦ ብቻ ነው የሚያሳየው» የሚል መልዕክት ነው።