የፍርድ ቤቱ ዉሳኔና ተቃዉሞዉ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 3 2005ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሁለት የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲ ባለሥልጣናት እና በሰባት ተባባሪዎቻቸዉ ላይ ያሳለፈዉን የቅጣት ዉሳኔ የኦሮሞ ፌደራሊስት ፓርቲ አጣጥሎ ነቀፈዉ።ትናንት ያስቻለዉ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኦነግ አባላት ያላቸዉን ዘጠኙን ተከሳሾች ከሰወስት እስከ አስራ-ሰወስት ዓመታት በሚደርስ እስራት ቀጥቷቸዋል።ከተፈረደባቸዉ ሁለቱ በቅርቡ የተዋሐዱት የኦሮሞ ብሄራዊ ኮንግረስና የኦሮሞ ፌደራሊስቲ ፓርቲዎች ባለሥልጣናት ነበሩ።የተዋሐደዉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ፓርቲ ፕሬዝዳት ዶክተር መረራ ጉዲና ቅጣቱን በሰላማዊና ሕጋዊ ትግል የሚያምኑ ፖለቲከኞችና ወጣቶችን ለማስበርገግ ያለመ ብለዉታል።ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሰ