የፊልም ሥራ በኢትዮጵያ
ዓርብ፣ የካቲት 6 2007ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ዉስጥ የሚሠሩና የሚመረቱ ፊልሞች ቁጥርና ጥራት እያደገ መምጣቱን አንድ ብሪታንያዊ የፊልም ጥበብ ባለሚያ አስታወቁ። ለንደን ዩኒቨርሲ ባዘጋጀዉ ሥብሰባ ላይ ሥለ ኢትዮጵያ ፊልም ያደረጉትን ጥናት ያቀረቡት ማይክል ቶማስ እንደሚሉት ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በ1997 የተሠሩት ፊልሞች 10 ብቻ ነበሩ። ከ1998 እስካሁን በተቆጠሩት ሰባት አመታት ግን ከአምስት መቶ በላይ ፊልም ተሠርቷል። ያም ሆኖ አጥኚዉ እንደሚሉት የፊልም ሥራ ኢትዮጵያ ዉስጥ ረጅም ዘመን ቢያስቆጥርም ብዛቱም ሆነ ጥራቱ ናጄሪያ፤ ግብፅ፤ እና ጋናን ከመሳሰሉ ሐገራት ጋር ሲወዳደር ግን አነስተኛ ነዉ። የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ድልነሳ ጌታነሕ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ