የፈረንሳይ ወታደሮች ቅሌት በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 23 2007ማስታወቂያ
በወቅቱ ፈረንሳይ ቀድማ ወታደሮችዋን በመላክ ሃገሪቱን ለማረጋጋት አስተዋፅኦ ማድረጓ ይታወሳል። ካለፈው መስከረም ወዲህ ደግሞ የአፍሪቃ ሰላም አስከባሪ ኃይል የፈረንሳይ ወታደሮችን በመተካት ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ከገባ ወዲህ 2 ሺህ የሚሆኑ ወታደሮችዋን ከሃገሪቱ ማስወጣት ጀምራለች። በጎርጎሮሳዊው ታህሳስ 2013 እስከ ሰኔ 2014 መካከል በሃገሪቱ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ተሰማርተው ከነበሩት የፈረንሳይ ወታደሮች አንዳንዶቹ በታዳጊ ወጣቶች ላይ የወሲብ ጥቃት መፈፀማቸውን የሚያጋልጥ ዘገባ ይፋ ከተደረገ በኋላ ጉዳዩ ማነጋገሩ ቀጥሏል።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ