የፈረንሳይ እና ጀርመን የግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያ
ዓርብ፣ ሐምሌ 1 2008ማስታወቂያ
ትናንት ማርሴይ ፈረንሳይ ውስጥ በተካሄደው የአውሮጳ እግር ኳስ ሻምፕዮና የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ጀርመንን 2 ለባዶ ያሸነፈው የፈረንሳይ ቡድን የፊታችን እሁድ ከፖርቱጋል ጋር የሚያካሂደው የፍጻሜ ጨዋታ በጉጉት እየተጠበቀ ነው ። የዘንድሮው ሻምፕዮና ማን ሊሆን ይችላል ለሚለው የተለያዩ ግምቶች እየተሰነዘሩ ቢሆንም ዋንጫውን ለአዘጋጇ ለፈረንሳይ የሚመኙ ብዙዎች ናቸው ። ለፍጻሜ ይደርሳል ተብሎ በሰፊው ይጠበቅ የነበረው የጀርመን ቡድን ትናንት ማታ ከፈረንሳይ ጋር ባከሄደው ግጥሚያ መሸነፉ ብቻ ሳይሆን አንድም ግብ ማግባት አለመቻሉ አስገርሟል ።ስለትናንቱ ጨዋታ ሂደት እና ውጤት የስፖርት ፕሮግራም አዘጋጅ ማንተጋፍቶት ስለሺን ኂሩት መለሰ አነጋግራዋለች ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ