የፈረንሳይ መንግሥትና ግብረ ሠናይ ድርጅቶች
ዓርብ፣ ሚያዝያ 18 2011ማስታወቂያ
የፈረንሳይ መንግስት ሥደተኞችን እያደኑ የሚይዙ የሊቢያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎችን ለማስታጠቅ መወሰኑን የተለያዩ የመብት ተሟጋቾችና የርዳታ ድርጅቶች ተቃወሙት።ፈረንሳይ የሊቢያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች ወደ አዉሮጳ የሚሻገሩ ስደተኞችን እየተከታተሉ ለመያዝ የሚገለገሉባቸዉ 6 ፈጣን ጀልባዎችና ወታደራዊ ትጥቆችን ለመሸጥ ከሊቢያ ጋር ተዋዉላለች።አምንስቲ ኢንተርናሽናልና ድንበር የለሽ ሐኪሞችን ጨምሮ ስምንት የመብት ተሟጋቾችና የርዳታ ድርጅቶች እንደሚሉት የፈረንሳይ መንግስት ዉሳኔዉን ካልሻረ በሕግ ይፋረዱታል።
ኃይማኖት ጥሩነሕ
ነጋሽ መሐመድ
ተስፋለም ወልደየስ