የጦር መሣሪያ ንግድ ቁጥጥር ውል
ረቡዕ፣ መጋቢት 25 2005ማስታወቂያ
ለረዥም ጊዜ ሲከራክር የቆየውን የጦር መሣሪያ ሽያጭና ዝውውር ቁጥጥር ረቂቅ ውል የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ትናንት አፅድቋል ። ረቂቁ ከ193 አባል ሐገራት የ154 ቱን ድጋፍ ሲያገኝ 3 አገራት ተቃውመውታል ። 23 ደግሞ ድምፃቸውን አቅበዋል ። ድምፃቸውን ካቀቡት ውስጥ ዋነኛዎቹ የጦር መሣሪያ ነጋዲዎች ሩስያ ና ቻይና እንዲሁም የጦር መሣሪያ ገዥዎች ግብፅና ህንድ ይገኙበታል ። ውሉን ከደገፉት አንዷ ዋነኛዋ የጦር መሣሪያ ነጋዴ አሜሪካን ስትሆን በአሜሪካን ውሉ መፅደቁ አጠራጣሪ መሆኑ ከወዲሁ እየተነገረ ነው ። ታሪካዊ ስለ ተባለው ስለዚሁ ውል ምንነትና ተፈጻሚነት የዋሽንግተን ዲሲውን ዘጋቢያችንን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
አበበ ፈለቀ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ