የጦማሪ እና አራማጅ ዘላለም ወርቅአገኘሁ መፈታት
ማክሰኞ፣ ጥር 22 2010ማስታወቂያ
በግንቦት 2008 ዓ.ም ሽብርተኝነት በመርዳት ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ የተፈረደበት ዘላለም ወርቅአገኘሁ የእስር ጊዜውን ጨርሶ የተለቀቀው በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር ካለው ከዝዋይ ማረሚያ ቤት ነው፡፡ ዘላለም በ2001 ዓ.ም. በወጣው የጸረ-ሽብር ህግን ተላልፋሃል በሚል የተፈረደበት አምስት ዓመት ከአራት ወር ነበር። በቂሊንጦ፣ ቃሊቲ እና ዝዋይ ማረሚያ ቤቶች ለ3 ዓመት ከ7 ወር በእስር የቆየው ዘላለም ዛሬ ተፈትቶ ከቤተሰቡ ጋር ተገናኝቷል። ከእስር ከወጣ ከጥቂት ሰዓት በኋላ በስልክ ለዶይቼ ቬለ የሰጠውን አጠር ያለ ቃለ ምልልስ የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ ፡፡
ተስፋለም ወልደየስ
ሂሩት መለሰ