የጥረት ኮርፖሬት የቀድሞ ሥራ አስፈፃሚ እንዲፈቱ በዋግኽምራ ሰልፍ ተጠየቀ
ቅዳሜ፣ መጋቢት 5 2012“ፍትህ ለምትኩ በየነ” የሚል ሰልፍ ዛሬ በሰቆጣ ከተማ መካሄዱን የዞኑ ኮመዙኒኬሽን መምሪያ አስታውቋል፡፡ አቶ ምትኩ በየነ፣ በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብየረሰብ ዞን በተለያዩ የስራ መስኮች የሰሩ ሲሆን ዞኑን በዋና አስተዳዳሪነትም ለብዙ ዓመታት መርተዋል፡፡
በጨረሻም በጥረት ኮርፖሬት የአምባሰል ንግድ ሥራዎች ድርጅት ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ ከሌሎች ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው ተጠርጥረው በባህር ዳር ማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታዬ ይገኛል፡፡
ግለሰቡ አፋጣኝ ፍትህ እንዲያገኝ በሚል ዛሬ በሰቆጣ ከተማ ሰልፍ መካሄዱን የዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ባለሙያ አቶ መብራቱ መኮንን ለዶይቼ ቬለ በስልክ ተናግረዋል፡፡
ሰልፈኞች ከያዟቸው መልእክቶች መከከል “ፍትህ ለምትኩ በየነ”፣ “አገራዊ ለውጡን እንደግፋለን”፣ ምትኩ በየነ ባህላችንም ልማታችንም ነው የሚሉ መልዕክቶች መስተጋባታቸውንም አመልተዋል፡፡
ከሰልፉ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ጌታቸው አሰፋ በስልክ እንደገለፁት “ግለሰቡ ከአንድ ዓመት በላይ በማረሚ ቤት ፍትህ አላገኘም አሁንም ፍትህ ሊያገኝ ይገባል” ብለዋል፡፡
አቶ ከደር አዳነ የተባሉ ሌላው የሰልፉ ተሳታፊ በበኩላቸው በሰልፉ ከሁሉም አካባቢዎች የተወከሉ ነዋሪዎች በሰልፉ መገኘቱንና እርሳቸውም ሰልፉን ደግፈው መውጣታቸውን አስረድተዋል፡፡
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተገኙት የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አሸብር ግርማ ህዝብ የጠቀውን ጥያቄ ለሚመለከተው አካል እንደሚያደርሱ በሰልፉ ላይ ባስተላለፉት መልእክት መግለፃቸውን ከዞኑ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መመሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ሰለፉ አንዲደረግ መጋቢት 1 ቀን 2012 ዓ ም በከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ በተፃፈ ደብዳቤ የተፈቀደ መሆኑን ዶይቼ ቬለ ማረጋገጥ ችሏል፡፡
ዓለምነው መኮንን
እሸቴ በቀለ