የዶክተር አሚር መግለጫ
ዓርብ፣ ግንቦት 2 2011ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር የተለማማጅም ይሁን አጠቃላይ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄዎች ምላሽ አግኝተዋል አለ። የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ ያልተመለሱት ቀሪ ጥያቄዎችም በሂደት የሚፈቱ ናቸው ብለዋል፡፡ የህክምና ተማሪዎች ማህበር ግን በሳምንቱ መጀመሪያ ለ DW አብዛኞቹ ጥያቄዎቻችን አልተፈቱም ሰላማዊው ትግላችንም ይቀጥላል ሲል አስጠንቅቆ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ሃገሪቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጤና ባለሞያ የምትፈልግ ቢሆንም በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ወደ ህክምና ትምህርት የሚገቡ ተማሪዎችን ቁጥር በመቀነስ የትምህርት ተቋማቱ የማስተማር ብቃትና ጥራት እንዲጣጣም ለማድረግ ታስቧልም ብለዋል ሚኒስትሩ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ጋዜጣዊ መግለጫውን ተከታትሎ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ