የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም እና የምሁራን ውይይት
እሑድ፣ መጋቢት 18 2008ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ልዩ ልዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን ጋር ያካሄዱት ውይይት አስፈላጊነትና ውይይቱ የተካሄደበት ወቅት እያነጋገረ ነው ። በውይይቱ የተወሰኑ ምሁራን ብቻ መሳተፋቸውም ጥያቄዎችን አስነስቷል ። አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ሥልጣን ከያዙ ሦስት ዓመት ተኩል ያለፋቸው አቶ ኃይለ ማርያም በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ምሁራንን ለማወያየት ዘግይተዋል ሲሉ ሌሎች ደግሞ ቢዘግይም መካሄዱ በራሱ ጥሩ ነው ይላሉ ። የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም እና የምሁራን ውይይት ፋይዳና አንድምታው የዛሬው እንወያይ ርዕስ ነው ። ሙሉውን ውይይት የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ ።
ኂሩት መለሰ
ልደት አበበ