የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቁ
እሑድ፣ ሐምሌ 17 2008ማስታወቂያ
በጎንደር አለመረጋጋቱም ሆነ ፍጥጫዉ እንዲከሰት ጥያቄያቸዉን በሰላማዊ እና ሕጋዊ መንገድ ለሚመለከታቸዉ የመንግሥት አካላት ያቀረቡ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት መታሰር ወይም የኮሚቴዉ አባላት እንደሚሉት ደግሞ ባልታወቁ ኃይሎች መታፈን ዋናዉ ምክንያት ነዉ። መንግሥት በበኩሉ ችግሩ የተከሰተዉ በሕጋዊ ጥያቄ ሽፋን የኢትዮጵያን ሰላም እና ልማት ለማደናቀፍ ከኤርትራ መንግሥት ጋር የሚላላኩ ኃይሎችን በቁጥጥር ሥር ለማድረግ የተደረገ እንቅስቃሴ እንደሆነ ይናገራል። የሰዉ ሕይወት መጥፋትንም ሆነ የንብረት ጉዳትን ያስከተለዉ ይህ ዉጥረት ወደ ብሔር ግጭት እንዳያመራ ስጋታቸዉን የሚገልፁ አሉ።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ «ኦዲዮውን ያዳምጡ» የሚለውን ይጫኑ።
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ