የጎሳ ግጭት በአፋር
ዓርብ፣ ሚያዝያ 2 2007ማስታወቂያ
በአፋር ክልል በአሚባራ ወረዳ ቦልሃም በተባለ ቦታ በሁለት ጎሳዎች መካከል በተነሳ ግጭት የሰዎች ህይወት አለፈ ። ዘጋቢያችን ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሄር ያነጋገራቸው የዓይን ምስክር በግጭቱ ከ10 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል ። የዓይን ምስክሩ እንደሚሉት ግጭቱ አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል ። የግጭቱ መንስኤ የግጦሽ ቦታ ይገባኛል ጥያቄ መሆኑን ተነግሯል ። በአፋርና በሌሎችም አካባቢዎች የሚነሱ መሰል ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴንና ዘመናዊ ህግን አጣምሮ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ዶቼቬለ ያነጋገራቸው አንድ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ተናግረዋል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ