የግንቦት ሐያ በዓልና የተቃዋሚዎች ቅሬታ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 20 2005ማስታወቂያ
የቀድሞዉ አማፂ ቡድን የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ግንባር (ኢሐዴግ) የቀድሞዉ የኢትዮጵያ መንግሥት አስግዶ ሥልጣን የያዘበት ሃያ-ሁለተኛ ዓመት ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች ዛሬ እየተከበረ ነዉ።ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዲግ በሚቆጣረቻዉ መገናኛ ዘዴዎች አማካይነት ባለፉት ሐያ-ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመሥረቱን፥ ፍትሕና ርትዕት መሥረፀን አስታዉቋል። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ተቃራኒዉን ነዉ የሚሉት።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ያነጋገራቸዉ የሰወስት ተቃዋሚ ፓርቲ ባለሥልጣናት እንደሚሉት የሃያ-ሁለት ዓመቱ ጉዞ የዴሞክራሲዊ ሥርዓት የተጓደለበት፥ ሙስና የሠፈነበት እና የኢሕአዴግ ባለሥልጣናትና ካድሬዎች የተጠቀሙበት ነዉ።ዝርዝሩን እነሆ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሠ