የግሪክ አፋጣኝ የምርጫ ዝግጅት
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 22 2007ማስታወቂያ
ለዚህ ዝግጅትም በዛሬዉ ዕለት መንግሥት የሀገሪቱን ምክር ቤት በትኗል። የግሪክ መንግሥት ሀገሪቱ ከገባችበት የኤኮኖሚ ቀዉስ እንድትወጣ በሚል ከዓለም ዓቀፍ አካላት የቀረበለትን የቁጠባ ስልት ተግባራዊ ለማድረግ መሞከሩ፣ ችግሩን ቀርፎ የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የፈየደዉ ባለመኖሩ ባለፉት ጊዜያት ሀገሪቱ በተቃዉሞ ስትናወጥ ቆይታለች። ስለግሪክ የምርጫ ዝግጅትና ዉስብስብ ችግሮች የብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ