የጋዜጠኛ ተመስገን ምሥክሮች ጉዳይ በፍርድ ቤት
ሐሙስ፣ ግንቦት 22 2005ማስታወቂያ
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ አሥራ ስድስተኛ ወንጀል ችሎት፤ ልደታ ምድብ፣በጋዜጠኛ ተመሥገን ደሳለኝ ላይ ክስ የመሠረተው ዐቃቤ -ህግ ፣ የመከላከያ ምሥክሮችን ቃል እንዳይሰማ ቢቃወምም፣ ፍርድ ቤቱ የሚከለክልቸው ህግ የለም በማለት መወሰኑ ተነግሯል። ፍርድ ቤቱ ፤ የጋዜጠኛ ተመሥገን ምሥክሮች የሆኑት ፕሮፌሰር መሥፍን ወ/ማርያምና ዶ/ር ያሬድ ለገሠ ለምሥክርነት ሊቀርቡ አይገባም በማለት ያመለከተውን ነው ውድቅ በማድረግ እንዲመሠክሩ የፈቀደው። ምሥክር የማዳመጡ ሂደትም ሐምሌ 2 ቀን 2005 እንዲጀመር ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል ።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ተክሌ የኋላ
ሂሩት መለሰ