የጊኒ ቢሳው ፕሬዚደንት ሞት
ቅዳሜ፣ ጥር 26 2004ማስታወቂያ
በ 2009 ዓም በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት የስድሳ አራት ዓመቱ ፕሬዚደንት ሳንሃ በተለይ በፖለቲካው ዘርፍ የጦር ኃይሉ ተፅዕኖ ከፍተኛ በሆነባት በጊኒ ቢሳው መረጋጋት የማምጣቱን ተግባር ዋነኛው ዓላማቸው አድርገው ነበር። የዶይቸ ቬለ ባልደረባ ሄለን ደ ጉቬያ እንደዘገበችው፡የሱስ አስያዥ ዕፅ ንግድ ያስፋፉት እና ለኮኬይን ንግድ ማጓጓዣው ተግባር ጊኒ ቢሳውን እንደ መተላለፊያ የተጠቀሙባትና አሁንም የሚጠቀሙባት የደቡብ አሜሪካ ሕገ ወጥ ቡድኖችም በዚችው ምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሀገር ውስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳርፈዋል። የዛሬው ዝግጅት ባለፉት ዓመታት በርካታ መፈንቅለ መንግሥት እና ግድያ የተካሄደባትን ጊኒ ቢሳው ለማረጋጋት ስለሞከሩት ማቹ ርዕሰ ብሔር ማላም ባካይ ሳንሃ ማን እንደነበሩ ባጭሩ ይመለከታል።
አርያም ተክሌ
መሥፍን መኮንን