የጊነዉ ፕሪዝደንት ሞትና ግልጽ ያልሆነዉ የአገሪቷ አስተዳደር
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 15 2001ማስታወቂያ
የምዕራብ አፍሪቃዊቷን አገር ለ24 አመታት የመሩት የ 74 አመቱ ፕሪዝደንት ላሳና ኮንቴን ከትናንት በስትያ ምሽት ላይማረፋቸዉ ከተሰማ ከሰአታት በኻላ የአገሪቱ የጦር ሰራዊት አዛዦች የመንግስት ተቋማት በሙሉ መፍረሳቸዉን በመግለጽ የመንግስት ግልበጣን አካሂደዋል ይህንን ተከትሎም የአፍሪቃዉ ህብረት የሰላም እና ጸጥታዉ ምክር ቤት ዛሪ አዲስ አበባ ላይ የዝግ ዉይይት መያዙም ተገልጾአል። ላሳና ኮንቴን በልብ ህመም የስዃር እና በደም በሽታ ህመም ለብ’ዙ ግዜ መሰቃየታቸዉ ይነገራል። የላሳና ኮንቴን ከባድ አጫሽም ነበሩ።