የጉራፈርዳ ተፈናቃዮች እሮሮ
ሐሙስ፣ ሰኔ 3 2013ማስታወቂያ
ከደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች መንግሥት ለደረሰብን ችግር መፍትሄ ይስጠን ሲሉ ጠየቁ። «ሕይወታችን አደጋ ላይ ወድቋል» በማለት ከጉራፈርዳ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ዛሬ ሀዋሳ በሚገኘው የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ደጃፍ በመሰባሰብ አቤቱታቸውን አሰምተዋል። ተፈናቃዮቹ አዛው ባሉበት የጉራፈርዳ ወረዳ እየተረዱ እንደሚገኙ ነው የማውቀው የሚለው የደቡብ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ ነዋሪዎቹ ቀደም ሲል ወደ መጡበት ዞን ስለመመለሳቸው አስከአሁን ያሳወቀው አካል እንደሌለ ገልጿል።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ