1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገዢዉ ፓርቲ ከተቃዋሚዎች ጋር የመነጋገር ዝግጁነት

እሑድ፣ ታኅሣሥ 9 2009

ኢትዮጵያ ዉስጥ ሕዝባዊ ተቃዉሞ ባየለበት ሰሞን  መንግስት ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እንደሚነጋገር ሲገልጽ ተሰምቷል። በዚህ ወቅትም በተለይ የምርጫ ሕግና ሥርዓቱን ዳግም ለመፈተሽ ብሎም ለማስተካከልም መዘጋጀቱንም ገልጾ ነበር።

https://p.dw.com/p/2UShG
Infografik Karte Proteste und Ausschreitungen in Äthiopien 2016

የጋራ ዉይይት

 በ2007 የተካሄደዉን ምርጫ ገዢዉ ፓርቲ መቶ በመቶዉ ድምጽ አሸንፌያለሁ ብሎ መንግሥት በመሠረተበት ወቅትም በዚህ ምርጫ ተቃዋሚዎች ወደ ምክር ቤት መግባት ባይችሉም፤ በአስፈላጊ ሀገራዊ ጉዳዮች ከእነሱ ጋር እመካከራለሁ የሚል ቃሉንም በይፋ ገልጾ ነበር። እስካሁን ግን አንዳቸዉም ተግባራዊ ሲሆኑ አልታዩም። የሀገሪቱ የፖለቲካ ትኩሳት የሚያሳስባቸዉ ወገኖች ደጋግመዉ መንግሥት ለዉይይት በሩን እንዲከፍት ጠይቀዋል። እየጠየቁም ነዉ። በእርግጥ ገዢዉ ፓርቲ ለእንዲህ ዓይነቱ ዉይይት ዝግጁ ነዉ? ዶይቼ ቬለ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንግዶችን ጋዝቦ አወያይቷል። ሙሉ ዉይይቱን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ!

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ