የገንዘብ ዋጋ መቀነስ
እሑድ፣ ነሐሴ 4 2006ማስታወቂያ
የዉጭ ምንዛሪ ፍላጎት ከፍ በሚልበት አጋጣሚ ደግሞ ይህ ጎልቶ ይታያል። የኤኮኖሚ ባለሙያዎች ይህን የፍላጎትና አቅርቦት ያለመመጣጠን ዉጤት ነዉ ይሉታል። ኢትዮጵያ ዉስጥ የአንድ ዶለር ምንዛሪ ከ2 ብር ከ40 ሣንቲም ተነስቶ፤ ባለፉት ዓመታት ከፍ እያለ ሄዶ አሁን 19 ብርን አልፏል። ኢትዮጵያ የምንዛሪ መጠኑን ከፍ ማድረጓን ብትቀጥል የብር የመግዛት አቅም እንዴት ሊሆን ይችላል? አንድ ሀገር መገበያያ ገንዘቡ ዋጋዉን ጠብቆ ለመዝለቅስ ምን ማሟላት ይጠበቅበታል? የዶቼ ቬለ የዚህ ሳምንት የዉይይት ርዕሰ ጉዳይ ነዉ።
ሸዋዬ ለገሠ
ልደት አበበ