የገንዘብ እርዳታ ለሰማዕታት ቤተሰቦች
ዓርብ፣ ሰኔ 26 2007ማስታወቂያ
በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከሁለት ወር በፊት ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ በሚጠራው ፅንፈኛ ቡድን ሊቢያ ውስጥ በአረመኔያዊ ግድያ ህይወታቸው ላለፈ ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት ወላጆች እና ቤተሰቦች ያሰባሰቡትን ገንዘብ አበረከቱ። ትናንት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቤተክህነት በተካሄደ ስነስርዓት ላይ እንደተገለፀው ስዊዝ ነዋሪ የሆኑት ኢትዮጵያውያን ሊቢያ ውስጥ በግፍ ለተገደሉት ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ሰማዕታት ቤተሰቦችና ወላጆች ከ400 ሺህ ብር በላይ ነው ያዋጡት። በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ