1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገና ገበያ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 26 2009

የኦርቶዶክስተዋሕዶ ክርስቲያኖች የገና በዓል  በመቃረቡ ነዉ መሰል ስኳር ቡታናጋዝንም ከገበያ ለማስኮብለል ሳያደባ አልቀረም።ገና መጣ፤ አዲስ አበባ ላይ ስኳር የለም።ጋዝም «አለ» ማለት ያስቸግራል

https://p.dw.com/p/2VGHP
Äthiopien Lebensmittel-Markt in Addis Ababa
ምስል DW/Y. Gebre-Egziabher

^M M T/ (Beri.AA) Gena.Market in AA - MP3-Stereo

ስኳር ይጣፍጣል።ሲበዛ ግን፤ ሐኪሞች እንደሚሉት፤ በሽታ ያመጣል። አዲስ አበባ ግን ይጣፍጣትም፤ በሽታ ያምጣባት፤ ስኳር እንደ ሩቅ ዘመን ቁስ ትዝታ እየሆነባት ነዉ-ያዩ እንደሚሉት። የኦርቶዶክስተዋሕዶ ክርስቲያኖች የገና በዓል በመቃረቡ ነዉ መሰል ስኳር ቡታ ጋዝንም ከገበያ ለማስኮብለል ሳያደባ አልቀረም። ገና መጣ፤ አዲስ አበባ ላይ ስኳር የለም። ጋዝም «አለ» ማለት ያስቸግራል። አለም፤ የለምም ማለትም-የለም። በተለይ ነዳጅ ማደያ አጠገብ። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ