የጀርመን ፕሬዝዳንቶች የጎላ ሚና
ማክሰኞ፣ ሰኔ 22 2002ማስታወቂያ
ለዚህ ምርጫ በዋነኛ ዕጩነት የቀረቡት የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ህብረት ፓርቲው በጀርመንኛው ምህፃር የ CDU ክርስቲያን ቩልፍ እንዲሁም የሶሻል ዲሞክራቶቹና እና የአረንዴዎቹ ፓርቲ ዕጩ ዮአሂም ጋውክ ናቸው ። ከሁለቱ ዕጩዎች በተለይ ቩልፍ የመመረጥ ዕድላቸው የሰፋ መሆኑ ከወዲሁ እየተነገረ ነው ። የጀርመን ፕሬዝዳንት በሀገሪቱ ፖለቲካዊ ዕንቅስቃሴዎች ውስጥ ያን ያህል የጎላ ሚና ሲጫወት አይታይም ። ምንም እንኳን የጀርመን ፕሬዝዳንት ተግባር በአብዛኛው ከስነ ስርዓታዊ ጉዳዮች የበለጠ ባይሆንም አንዳንዶቹ ግን በሐገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠውን ዕርምጃ በመውሰድ ይታወሳሉ ። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን አንዱ ትኩረት ነው ።
ሂሩት መለሰ
ነጋሸ መሐመድ