የጀርመን ፍርድ ቤቱ ዉሳኔና ፖለቲከኞች
ረቡዕ፣ መስከረም 2 2005ማስታወቂያ
የጀርመን መንግሥት ለከሠሩ የዩሮ ሸርፍ ተጠቃሚ ሐገራት መደጎሚያ የሚሆነዉ መጠባበቂያ ገንዘብ ማዋጣቱን የሚቃወሙ ወገኖች ያቀረቡትን አቤቱታ የሐገሪቱ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ዉድቅ አደረገዉ።ካርልስሩኸ-ያስቻለዉ ፍርድ ቤት ባሳላፈዉ ዉሳኔ መሠረት የጀርመን ምክር ቤት ካፀደቀዉ የሐገሪቱ መንግሥት ለአዉሮጳ የማረጋጊያ ሥርዓት (ESM) ለተሰኘዉ ተቋም አንድ መቶ ዘጠና ቢሊዮን ዩሮ ድረስ ያለ ብዙ ቅድመ ሁኔታ ማበደር ወይም የብድር ዋስትና መስጠት ይችላል።የፍርድ ቤቱ ዉሳኔ የጀርመን ተጣማሪ መንግሥት ፖለቲከኞችን ሲበዛ ነዉ ያስደሰተዉ። ቮልፍጋንድ ላንድሜሰር የዘገበዉን ይልማ ሐይለ ሚካኤል አጠናቅሮታል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሰ