የጀርመን ግንብ መዉደቅና የአፍሪቃ ፖለቲካ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 27 2012ማስታወቂያ
የካፒታሊስትና የሶሻሊስት ርዕዮተ-ዓለም ልዩነት በዉጤቱም የቀዝቃዛዉ ጦርነት ፍጥጫ ምልክት ተደርጎ ይታይ የነበረዉ የበርሊን ግንብ ከፈረሰ ትናንት 30ኛ ዓመቱን ደፈነ። አሜሪካዊዉ የፖለቲካ ሳንቲስት ፍራንሲስ ፋኩያማ የግንቡን መንደርመስ አስመልክተዉ «የታሪክ መጨረሻ» የሚል ዝነኛ መፅሐፍ አሳትመዉም ነበር። የግንቡ መናድ የሶሻሊስቱ ርዕዮተ ዓለም ፍፃሜ በመሆኑ ኢትዮጵያን ጨምሮ ርዕዮተ-ዓለሙን ይከተሉ በነበሩ የአፍሪቃ ሐገራትን ጭምር አዲስ ሥርዓት እንዲያማትሩ አስገድዷቸዋል። የዛሬዉ አዉሮጳና ጀርመን ዝግጅታችን የዛሬ 30 ዓመቱን ሁነት መለስ ብሎ ይቃኛል።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚከተለዉ አጠናቅሮታል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ