1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ያገለገሉ መኪናዎች

ረቡዕ፣ ነሐሴ 6 2001

እዚህ ጀርመን ሀገር መንግስት ሰዎች ከአምስት ዓመት በላይ ያገለገሉ አዉቶሞቢሎችን መልሶ ጨፍልቆ ለሌላ ተግባር እንዲዉሉ ለሚያደርገዉ ድርጅት ቢሰጡ አዲስ መኪና እንዲገዙበት የሚረዳ 2,500 ዩሮ ለመስጠት ቃል ገብቷል።

https://p.dw.com/p/J8V9
መኪኖቹ ሊጨፈለቁ ተሰባስበዋልምስል AP

በዚሁ መሠረትም በአፍሪቃ ብቻ ሳይሆን በምሥራቅ አዉሮጳ አንዳንድ ሀገራት ሳይቀር በአዲስነት ተገዝተዉ ጎዳናዉን ሊያጣብቡ የሚችሉትን አዉቶሞቢሎች ባለቤቶቻቸዉ ለዚህ ለሚጨፈልቀዉ ድርጅት እየሰጡ ገንዘብ ተቀብለዋል። መኪናዎቹ እጅግ ዘመናዊ የሚባሉ፤ ዉድ፤ ለተለያየ ጉዳይ የሚጠቅሙ ኤሌክትሮኒክሶች የተገጠሙላቸዉ፤ 50,000 ግፋ ቢል ከ100,000 ኪሎ ሜትር በላይ ያልተጓዙ መሆናቸዉንም ከጀርመን ያገለገሉ መኪናዎችን እየገዙ ወደአፍሪቃ የሚልኩት ነጋዴዎች ይገልጻሉ። ይህ ዜና እንደተሰማና ተግባሩም እንደተጀመረ ወደአፍሪቃ ሰልባጅ መኪና የሚልኩት ነጋዴዎች ቅሬታ ብቻ ሳይሆን ድንጋጤም ገጥሟቸዋል። ሰሞኑን የተሰማዉ ደግሞ ሌላ ታሪክ ነዉ። ሊጨፈለቁ እየተፈረደባቸዉ ገንዘብ የተበላባቸዉ አዉቶሞቢሎች ወደአፍሪቃ ገብተዋል።

ይልማ ኃይለሚካኤል/ሸዋዬ ለገሠ