1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን የኃይል ፍላጎትና ሩስያ

ዓርብ፣ ግንቦት 26 2003

ጀርመን መንግሥት እስከ ዛሬ 10 ዓመት ድረስ የአቶም ኃይል ማመንጫዎችን መጠቀም መሉ በሙሉ ለማቆም ማቀዱን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ አስታውቋል ።

https://p.dw.com/p/RRaL
ምስል RIA Novosti

ይህም ከአውሮፓ ትልቅ ምጣኔ ሐብት የምታንቀሳቅሰውን ጀርመንን ከውጭ የሚገባ ኃይል ጥገኛ ያደርጋታል ። በ10 ዓመታት ገደማ ጀርመን አካባቢን ብዙ ከማይበክል ምንጭ በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል ታገኛለች ። ባለሞያዎቹ አረንጓዴ የሚሉት ይህ የኤሌክትሪክ ኃይል በስፋት ጥቅም ላይ መዋል እስኪጀምር ግን ሃገሪቱ ብዙ አዳዲስ የጋዝ ኃይል ማመንጫ አማራጮችን ማግኘት ይኖርባታል ። ይህ ደግሞ ለጀርመን ጋዝ የምታቀርበዋን ሩስያን አስደስቷል ።

ክርስቲና ናግል

ሂሩት መለሰ

ሸዋዮ ለገሰ