የጀርመን ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ውህደት
ዓርብ፣ የካቲት 11 2003ማስታወቂያ
እነዚህ የጀርመን የልማት ድርጅቶች ኢትዮዽያ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ በተናጠል፤ ፕሮግራምና ወጪያቸውም ለየብቻ ሆኖ ቆይቷል። ይህ አካሄድ የገንዘብ ብክነትንና የፕሮግራሞች መደራረብን በማስከተሉ በአንድ ድርጅት ጥላ ስር እንዲሆኑ ከሰሞኑ ተወስኗል። የጀርመን ዓለም ዓቀፍ የትብብር ድርጅት ወይም ጂ.አይ.ዜድ በመባል ከዚህ በኋላ በአንድነት የሚጠቃለሉት የጀርመን ድርጅቶች አቅማቸውን አስተባብረው ለተሻለ ስራ እንደተነሱ አዲስ አበባ ያለው የጀርመን ኤምባሲ የሰጠው መግለጪያ ላይ ተገልጿል።
ጌታቸው ተድላ
መሳይ መኮንን
ተክሌ የኋላ