የጀርመን እገዛ ኢትዮጵያውያን ተመላሾች
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 20 2005ማዕከሉ በተለይ እውቀትና የሥራ ልምድ ያካበቱ ምሁራን ወደ ሃገራቸው ተመልሰው በሚፈለጉባቸው የሥራ መስኮች እንዲያገለግሉ ማድረግ ዋናው ትኩረቱ ነው ። ከጀርመን ወደ ኢትዮጵያ በፍላጎታቸው ለሚመለሱ ኢትጵያውያን ምሁራን እገዛ የሚያደርገው የጀርመን አለም አቀፍ የፍልሰትና የልማት ማዕከል የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ። ማዕከሉ ስለ ሚያከናውናቸው ተግባራት የኢትዮጵያው ቅርንጫፍ የፍልሰትና የዳይስፖራ መርሃ ግብር ሃላፊ ወይዘሮ ኮከቤ ኃይለ ገብርኤል ።
የጀርመን አለም አቀፍ የፍልሰትና የልማት ድርጅት በምህፃሩ CIM የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ የፍልሰትና የዳይስፖራ መርሃ ግብር ሃላፊ ወይዘሮ ኮከቤ ኃይለ ገብርኤል መስሪያ ቤታቸው ለነማን እገዛ እንደሚያደርግ የተናገሩት ። የጀርመን አለም አቀፍ የፍልሰትና የልማት ማዕከል እጎአ ከ2004 አመተ ምህረት አንስቶ በፍላጎታቸው ወደ ሃገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጰያውያንን በማገዝ ላይ ይገኛል ። ማዕከሉ በተለይ እውቀትና የሥራ ልምድ ያካበቱ ምሁራን ወደ ሃገራቸው ተመልሰው በሚፈለጉባቸው የሥራ መስኮች እንዲያገለግሉ ማድረግ ዋናው ትኩረቱ ነው ። በጀርመን አለም አቀፍ የትብብር መስሪያ ቤት በምህፃሩ ጂ.አይ.ዜድ እንዲሁም ከፌደራል ጀርመን የጀርመን የስራ ቅጥር ጉዳይ መስሪያ ቤት በትብብር ሥራውን የሚያካሂደው ይህ ማዕከል በተለይ ትኩረት የሚሰጣቸው የሙያ መስኮች አሉ ።
ወይዘሮ ኮከቤ እንደሚሉት ጀርመን አገር የተማረም ሆነ የሰራ ኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ተፈላጊ ነው ። በማዕከሉ የሚረዱት ግን መስፈርቶቹን የሚያሟሉ ናቸው ።
በኢትዮጵያ ምሁራን የሚፈለጉባቸው የተለያዩ የስራ መስኮች አሉ ። ሆኖም እንደ ወይዘሮ ኮከቤ ምሁራን በብዛት የሚፈለጉባቸው የሙያ መስኮች በየአመቱ ሊለያዩ ይችላሉ ።
እንደ ወይዘሮ ኮከቤ አሁን ደግሞ በብዛት የሚፈለጉት የስራ አመራር እውቀትና ልምዱ ያላቸው ባለሞያዎች ናቸው ሆኖም ከጀርመን የተመለሱ ምሁራን በሙሉ እንደሚፈለጉት ወይም የሚጠበቁትን ያህል ሆነው ላይገኙም ይችላሉ ።
የጀርመን አለም አቀፍ የፍልሰትና የልማት ድርጅት ኢትዮጵያን ጨምሮ በ18 አገራት ተመሳሳይ ተግባር ያከናውናል ።
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ