ጀርመን እና ቱርክ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 13 2009ማስታወቂያ
የጀርመን እና የቱርክ ውዝግብ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ጀርመን ወደ ቱርክ የሚጓዙ ዜጎቿ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ዛሬ አሳስባለች። የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዚግማር ጋብርየል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን በምታስረው በቱርክ እያንዳንዱ የጀርመን ዜጋ ተመሳሳይ እጣ ሊገጥመው እንደሚችል ዛሬ ተናግረዋል። ጋብርየል ቱርክ ጀርመናዊ ፔተር ስቶይድነርን እና ሌሎች 5 የመብት ተሟጋቾች ማሰሯ በአንካራ ላይ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ማስከተሉ እንደማይቀር አስጠንቅቀዋል። ስለሁለቱ ሀገራት ውዝግብ የበርሊኑን ወኪላችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ