የጀርመን ኢትዮጵያውያን ማህበር
ማክሰኞ፣ ጥር 7 2005
የጀርመን ኢትዮጵያውያን ማህበር ከተመሰረተ ባለፈው መስከረም 17 አመት ሆኖታል ። የተመሰረተውም ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያየ የሙያ መስክ ይሰሩ በነበሩ ጀርመናውያን ነው ። ጀርመናውያኑ ማህበሩን የመሰረቱትም ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለመቀጠልና ስለ ኢትዮጵያም መረጃ ለመስጠት በማሰብ ነው ። በጥቂት ጀርመናውያን የተቋቋመው ይህ ማህበር ብዙም ሳይቆይ ኢትዮጵያውያንን አባላትንም አሰባሰበ ። የማህበሩ የቦርድ ፀሃፊ አቶ መስፍን አማረ ለዲቼቬለ እንደተናገሩት ማህበሩ በአሁኑ ጊዜ 125 አባላት ሲኖሩት ከመካከላቸው 30 ያህሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው ። የማህበሩ ዋነኛ አላማ ኢትዮጵያን ለጀርመናውያን ማስተዋወቅ ነው ። ለዚሁ ተግባርም ኢትዮጵያን የተመለከቱ መረጃዎችን በአመት 3 ጊዜ በሚያወጣው መፅሄትና በአመት አንድ ጊዜ በሚጠራው ጉባኤ አማካይነት ያቀርባል ። ለመሆኑ ማህበሩ ስለ ኢትዮጵያ የሚሰጣቸው መረጃዎች ምን ላይ ያተኮሩ ናቸው ? አቶ መስፍን
የጀርመን ኢትዮጵያውያን ማህበር አቅም በፈቀደ መጠን የተቋቋመበትን ዓላማ ተግባራዊ በማድረግ ላይ መሆኑን አቶ መስፍን ይናገራሉ ። አቶ መስፍን ማህበሩ በ17 አመታት ውስጥ ካከናወናቸው ተግባራት አብይ የሚሏቸውን ገልፀዋል ።
የጀርመን ኢትዮጵያውያን ማህበር የዘንድሮው ጉባኤው እንደሁልጊዜው በካስል ከተማ በሚያዚያ አጋማሽ ላይ ያካሂዳል ። ከጉባኤው ትኩረቶች አንዱ የኢትዮጵያ የቱሪዝም እንቅስቃሴ እንዲሁም ጥቅምና ጉዳቱ ነው ። ጉባኤተኞችም የኢትዮጵያ ተሞክሮአቸውን እንዲሚያካፍሉ አቶ መስፍን ተናግረዋል ።
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ