የጀርመን ቀኝ ፅንፈኛ ፓርቲ
ዓርብ፣ ኅዳር 28 2005ማስታወቂያ
በጀርመንኛ ምሕፃሩ NPD ተብሎ የሚጠራዉ የጀርመን ቀኝ ፅንፈኛ ፓርቲ እንዲታገድ የ16ቱም የሐገሪቱ የፌደራል ክፍለ-ሐገራት ጠቅላይ ሚንስትሮች ትናንት ተስማምተዋል።ከጠቅላይ ሚንስትሮቹ በፊት የአገር አስተዳደር ሚንስትሮች ፓርቲዉ እንዲታገድ ተስማምተዉ ነበር።የፌደራሉ የሐገር አስተዳደር ሚንስትር ግን ፓርቲዉ ይታገድ መባሉ ተቀባይነት ማግኘቱን ይጠራጠራሉ።ያም ሆኖ በመጪዉ ሳምንት የሕግ መወሰኛዉ ምክር ቤት በሐሳቡ ላይ ተወያይቶ ፓርቲዉ የሚታገድበት ሒደት በሕገ-መንግስታዊዉ ፍርድ ቤት ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።ሥለ ጉዳዩ ሸዋዬ ለገሠ የበርሊኑን ወኪላችንን ይልማ ሐይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግራለች።
ይልማ ሐይለ ሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ