1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ሽልማት፧ ለጋናዊው ፍራንስስ አፒያ፧

ሐሙስ፣ መስከረም 30 2000

Deutsche Afrika Stiftung የተሰኘው የዴሞክራሲ አበራታች ድርጅት እ ጎ አ ከ 1993 ዓ ም አንስቶ፧ በአፍሪቃ ክፍለ-ዓለም፧ ዴሞክራሲ ሰላምና ሰብአዊ መብት ሥር እንዲሰድ ለሚታገሉ ግለሰቦች ሽልማት ሲሰጥ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

https://p.dw.com/p/E0aM
ምስል AP
ባለፉት ጊዜያት ከተሸለሙት መካከል፧ የሴት ልጆች ግዝረት እንዲቀር የምትታገለው ሶማሊያዊቷ ዋሪስ ዲሪ፧ በኤይድስ ዙሪያ ምርምር የሚያደርጉት የቦትስዋናው ጆን ጊቶንጎ ነበሩ ሽልማት የተቀበሉት። የዘንድሮው ተሸላሚ ደግሞ ጋናዊው ፍራንስስ አፒያ ናቸው። የዘንድሮውን ተሸላሚ ተግባራት አስመልክቶ የዶቸ ቨለ ባልደረባ Alexander Göbel ያቀረበውን ጽሑፍ ተክሌ የኋላ እንደሚከተለው ሰብሰብ አድርጎ አቅርቦታል።
በተበበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም የሚሠሩት፧ ጋናዊው ፍራንስስ አፒያ፧ ትናንት በርሊን ውስጥ የዘንድሮውን የጀርመን የዴሞክራሲ ማነቃቂያ ሽልማት የተቀበሉት፧ African Peer Review Mechanism በተሰኘው የአፍሪቃውያን የዴሞክራሲ እንቅሥቃሴ በጥሞና በመመርመር ረገድ በጋናና በብዙ የአፍሪቃ አገሮች አወንታዊ ሂደት እንዲከሠት በማብቃታቸው ነው። ማለፊያ አስተዳደር የሚባለው ዘዬ አፍሪቃን በተመለከተ ተዘውትሮ የሚነገረው ሙስና፧ የሥልጣን ብልግናና የመሳሰሉት የተንሠራፉ በመሆናቸው ነው። ስለሆነም፧ ዴሞክራሲን መገንባት፧ የተሃድሶ ለውጥን ማሥፋፋት ይቻል ዘንድ እርዳታ አቅራቢ አገሮች ለመተባበር የልማት እርዳታ ለመሥጠት፧ ገንዘብንም ሥራ ላይ ለማዋል ቃል መግባታቸው አልቀረም። ማለፊያ አስተዳደር፧ የእርዳታ ለጋሽ መንግሥታት ቋንቋ ብቻ ሆኖ አልቀረም። ራሳቸው አፍሪቃውያን ለጥቅማቸው ሲሉ የራሳቸውን «የቤት ሥራ« መሥራት እንዳለባቸው ከተገነዘቡ ውሎ አድሮአል። ይህን፧ አልክሳንደር ገኧበል እንደሚለው አዲስ አጋርነት ለአፍሪቃ ልማት(NEPAD) በተሰኘው እንቅሥቃሤ በኩል ጥረት ያደርጋሉ። ይህ የአፍሪቃን ኅብረትም የሚመለከት ነው። የአፍሪቃ መንግሥታት እርስ በርስ፧ አንዱ የሌላውን ጥረት እንዲገመግም ዓላማ አድርገው መነሣታቸውም ይነገራል። አንድን ሀገር፧ የሆነው ሆኖ በማኅበራዊ ኑሮና በኤኮኖሚ ለማራመድ፧ መሠረቱ፧ የአስተዳደር መሻሻል ነው። የአፍሪቃ ፖለቲከኞች፧ ይህ መሠረታዊ ጉዳይ ገብቷቸው ከህዝቡም የሚደረገው ግፊት ለሥራ እንዲንቀሳቀሱ ያበቃቸው፧ የጋናዊው የአስተዳደር ምሁር፧ የፍራንስስ አፒያ ጥረት መሆኑ ይነገራል። የሃምሳ ዓመቱ ጎልማሣ ፍራንስስ አፒያ፧ ባደረጉት ያላሠለሠ ጥረት፧ አክራ፧ ጋና፧ ውስጥ፧ በሚገኘው የ «ኔፓድ« ጽህፈት ቤት በኩል እርስ-በርስ በመረራከር ረገድ አገራቸው ጋኣአርአያ እንድትሆን አብቅተዋል። ለፍትኅና ለዕድገት መሻሻል፧ የእርስበርስ ግምገማ የሚያደርጉት የአፍሪቃ አገሮች ቁጥር አሁን 26 ደርሷል። በዚህ ተግባራቸውም ነው አፒያ ለሽማት የበቁት። ለእኒህ የጥሩ አስተዳደር ጠበቃም ሆነ ታጋይ ሽልማት ሲሰጥ፧ የጀርመን መራኂተ-መንግሥት ወይዘሮ አንጌላ ሜርክል፧ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል።
«ለአፍሪቃ የወደፊት ዕጣ፧ በራሳቸው መቆም ለሚችሉ መንግሥታት፧ ለዴሞክራሲ፧ ፍትኅና ፀጥታ፧ ለስኬታማ ኤኮኖሚም ቁልፉ ፍትኀዊ አመራስ ነው። ስለዚህ በመጻ ኀላፊነት መውሰድን ማለፊያ ነው ብዬ እደገፈዋለሁ። በርከት ያሉ አገሮች፧ በአፍሊቃ የአሠራር ደንብ፧ እርስ-በርስ የፖለቲካ መርኀቸውን በመፈተሽ፧ Africanö Peer Review Mechnism በተሰኘው ደንብ አዲስ መንገድ ለመጓዝ ኅብረተሰቡ ይበልጥ እንዲሳተፍ የ,ሚደረግበትን ኀላፊነት መሸከም፧ ግልፅ አሠራርና በይፋ የሚታይ የተሻለ የኑሮ ዘዴን የሚያመላክት እንዲሆን ያሻል።«
ፍራንስስ አፒያ፧ « አፍሮ ጨለምተኞች የምንላቸው አሉ። ምንም ለውጥ አይገኝም ብለው የሚያስቡ! እኔ ለውጥ አይቼአለሁ። መሥክሬአለሁ ሰዎች ለለውጥ ምንጊዜም ዝግጁ ናቸው። ስለሆነም፧ ብሩኅ አመለካከት ነው ያለኝ፧« ብለዋል።