የ«ጀርመንዊንግስ» አይሮፕላን አደጋ መንሥዔን የማጣራቱ ሥራ
ረቡዕ፣ መጋቢት 16 2007ቤልጅየም፣ ኢራን፣ አውስትሬሊያ፣ እስራኤል፣ ሜክሲኮ፣ ቬኔዝዌላ፣ ኮሎምቢያ፣ አርጀንቲንያ፣ ጃፓን እና የዩኤስ አሜሪካ ዜጎችም ይገኙበታል። የጀርመን ካቢኔ ሟቾቹን ዛሬ በአንድ ደቂቃ የኅሊና ፀሎት ከማሰቡ ጎን፣ በሀገሪቱ ሰንደቃላማዎች በግማሽ እየተውለበለቡ ነው። ስጳኝም የሶስት ቀናት ሀዘን አውጃለች።
አይሮፕላኑ በምን ምክንያት እንደወደቀ መረጃ ሊሰጥ የሚችለው ንዑስ ጥቁር ሣጥን ብልሽት ቢያጋጥመውም መጠቆሙ አይቀርም ይሆናል ሲሉ የፈረንሳይ የሀገር አስተዳደር ሚንስቴር ፣ ሚንስትር ደኤታ አላ‘ ቪዳሊስ ገልጸዋል።
ወድቆ በተከሰከሰው ጀርማን ዊንግስ ተሳፍረው የነበሩት አብዛኞቹ ፤ በጀርመን ፣ የኖርድራይን ቬስትፋለን ፌደራል ክፍለ ክፍለ ሀገር ተወላጆች ሲሆኑ ፤ 16 ቱ ለትምህርት ልውውጥ ሃልተርን ከተባለች ንዑስ ከተማ ባርሴሎና ደርሰው በመመለስ ላይ የነበሩ ለጋ ወጣቶች ነበሩ። የሐልተርን ከተማ ከንቲባ ቦዶ ክሊምፐል ፣
«ከተማይቱ በሐዘን መዋጧን መናገር እፈልጋለሁ። በየሥፍራው ብርቱ ድንጋጤና ሐዘን ነው ከሰው ፊት የሚነበበው።ያጋጠመው ሁኔታ እጅግ አስከፊ መሆኑን ማንም መገመት ይችላል።»
በፈረንሳይ የተከሰተውን የአይሮፕላን አደጋ ለማጣራት እየተደረገ ስላለው ርምጃ የፓሪሷን ወኪላችን ሀይማኖት ጥሩነህን ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት በስልክ አነጋግሪያት ነበር።
ሀይማኖት ጥሩነህ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ