የጀርመንና የዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነት
ሰኞ፣ ሐምሌ 7 2006ማስታወቂያ
በስለላ ከሚገኙ መረጃዎች የመጠቃቀሙ የተጓዳኝነት ምስጢር ልዉዉጥ እንዳለ ሆኖ አንዱ መንግስት ሌላዉን በማይገምተዉ መንገድ መሰለሉ የጀርመንን ፖለቲከኞች ማነጋገሩን ቀጥሏል። ለረዥም ዓመታት ዩናይትድ ስቴትስና ጀርመን እጅግ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸዉ ተጓዳኞች በመሆናቸዉም ዘመን በተሻገረዉ ጉድኝታቸዉ ላይ ተፅዕኖ ሊኖረዉ ይችል አይችል እንደሁ ግን ዝምታን በመረጠችዉ ዋሽንግተንና ምላሽ እንዲሰጣት በምትወተዉተዉ በርሊን መካከል ለጊዜዉም ቢሆን መጠራጠርን ያስከተለ መስሏል። የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለስልጣን ግን ትናንት ምንም ቢፈጠር ትስስሩ እንደማይበጠስ ነዉ ያመለከቱት። ሸዋዬ ለገሠ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘዉ ወኪላችን አበበ ፈለቀን በጉዳዩ ላይ በስልክ አነጋግራዋለች።
አበበ ፈለቀ
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ