የጀርመንና የቱርክ ግንኙነት
ሐሙስ፣ የካቲት 23 2009ማስታወቂያ
የጀርመንና የቱርክ ፖለቲከኞች የገጠሙት እስጥ አገባ ባለፉት ጥቂት ቀናት እየተካረረ ነዉ።የቱርክ መንግስት አንድ ጀርመናዊ ቱርካዊ ጋዜጠኛን ከሳረ ወዲሕ የተካረረዉ ዉዝግብ ዛሬ ደግሞ የቱርክ የፍትሕ ሚንስትር ጀርመን ዉስጥ ንግግር ለማድረግ ሲሞክሩ በመታገዳቸዉ ይበልጥ ተባብሷል።ታዛቢዎች እንደሚሉት የሁለቱ ሐገራት ፖለቲከኞች የገጠሙት ዉዝግብ መባባስ አጥብቀዉ የሚፈላለጉትን ሐገራት ግንኙነት ሊያዉከዉ ይችላል።ሥለ ጀርመንና ቱርክ ዉዝግብ የበርሊን ወኪላችን ይልማ ይልማ ኃይለሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ