የጀርመኑ ፕሬዝደንት የትምሕርት ቤት ጉብኝት
ማክሰኞ፣ ጥር 21 2011ማስታወቂያ
ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፍራንክ-ቫልተር ሽታይማየር ዛሬ ላሊበላን ጎብኝተዋል። ሽታይንማየር ከአዲስ አበባ ወደ ላሊበላ ከመጓዛቸዉ በፊት አዲስ አበባ የሚገኘዉን የፌደራል የቴክኒክ ሙያ ትምሕርትና ሥልጠና ተቋማን ጎብኝተዉ ነበር።በጀርመን መንግስት ድጋፍ የሚያስተምረዉ ተቋም በጥቅሉ ዘጠኝ ሺሕ ያክል ተማሪዎችን በተለያዩ ሙያዎች ያሰልጥናል።ሽታይንማየር ተቋሙን ሲጎበኙ ተማሪዎችና ኃላፊዎች ሥለተቋሙ ሥራና አሰራር ገለፀና ማብራሪያ አድርገዉላቸዋል።
ጌታቸዉ ተድላ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ