1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሜሪካ ጉብኝት

ዓርብ፣ ጥቅምት 27 2002

የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጌዶ ቬስተቬለ እና የአሜሪካዉ አቻቸዉ ሄላሪ ክሊንተን በትናንትናዉ እለት ዩናይትድ ስቴትስ ዋሽንግተን ዲስ ላይ ተገናኝተዉ በጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

https://p.dw.com/p/KQ5R
ምስል AP

ሁለቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በአለም የኢኮነሚ ቀዉስ፣ በአየር ጸባይ ለዉጥ፣ በአሸባሪነት እንዲሁም በኒኩሊየር ቅነሳ ዙርያ የጋራ አቋም መያዛቸዉን ከዉይይታቸዉ በዃላ በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸዉ ተገልጾአል። ዝርዝሩን ወኪላችን አበበ ፈለቀ ከዝያዉ ከዋሺንግተን ዲሲ ልኮልናል።

አበበ ፈለቀ፣ አዜብ ታደሰ፣ ነጋሽ መሃመድ