የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር በመካከለኛዉ ምሥራቅ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 30 2001ማስታወቂያ
የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር በመካከለኛዉ ምሥራቅ የሚያደርጉትን ጉብኝት ዛሬም እንደቀጠሉ ነዉ።ትናንት እየሩሳሌም ዉስጥ ከእስራኤል ባለሥልጣናት ጋር የተነጋገሩት ጀርመናዊዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ዛሬ ደማስቆ ዉስጥ ከሶሪያ፥ ቤይሩት ደግሞ ከሊባኖስ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ይልማ ሐ/ሚካኤል፦ ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሐመድ