የዶይቼ ቬለዋ ንጋት ከተማ
ሐሙስ፣ መጋቢት 3 2007ማስታወቂያ
« ላላፉት 10 ዓመታት የአድማጮች ማሕደርን ያዘጋጀችው ንጋት ከተማ። የዶይቼ ቬለዋ ንጋት ከተማ በርካታ አድማጮች አልዋት ብዙዎች እስታንፋሳችን ብርኃናችን ሲሉም ከልብ ያወድሷታል። የአድማጮች ማሕደር አዘጋጅ ንጋት ከተማን። ከ 28 ዓመት የአገልግሎት ዘመን በኋላ ከጥቂት ቀናት በፊት ከዶይቼ ቬለ በጡረታ የተሰናበተችዉ ንጋት ከተማ የአድማጮች ማኅደር እንግዳችን አድርገን ይዘናታል። በመግቢያዉ ላይ ከዝግጅቱ መለየትዋን ያሳደረባትን ስሜት ነበር የገለፀችልን። በዚህ ዝግጅት ወ/ሮ ንጋት ከተማ በዶይቼ ቬለ አገልግሎትዋ በተለይም ባለፉት 12 ዓመታት ያለማቋረጥ ያዘጋጀችዉን የአድማጮች ማኅደር ዝግጅት ትዝታዎችዋን ታካፍለናለች መሉ ቅንብሩን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ