1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶናልድ ትራምፕ ጸያፍ ንግግርና በዩኤስ ነዋሪዎች እይታ

ዓርብ፣ ጥር 4 2010

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ንግግር የአፍሪቃ ኅብረትን ብቻ አይደለም ያስቆጣው አሜሪካን ጨምሮ የመላው ዓለም መነጋገሪያ ኾኗል። ፕሬዚዳንቱ ንግግራቸውን ወደ ተግባር በመተርጎም የዲቪ ሎተሪን ለማጠፍ ዛሬ በዝግ ስብሰባ መቀመጣቸውም ተገልጧል።

https://p.dw.com/p/2qmPl
USA - Präsident Trump PK
ምስል Getty Images/M. Wilson

የዶናልድ ትረምፕ ጸያፍ ንግግርና በአሜሪካ ያስነሳው ቁጣ

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ንግግር የአፍሪቃ ኅብረትን ብቻ አይደለም ያስቆጣው አሜሪካን ጨምሮ የመላው ዓለም መነጋገሪያ ኾኗል። ፕሬዚዳንቱ ንግግራቸውን ወደ ተግባር በመተርጎም የዲቪ ሎተሪን ለማጠፍ ዛሬ በዝግ ስብሰባ መቀመጣቸውም ተገልጧል። የፕሬዚዳንቱ አስተዳደር መቀመጫ በኾነችው ዋሽንግተን ውስጥ ነዋሪ የኾኑ መጤዎች እና የውጭ ሃገር ዝርያ ያላቸው ነዋሪዎች ጸያፉን ንግግር በተመለከተ ምን አሉ? የመገናኛ አውታሮችና የፖለቲከኞች አጸፌታስ ምን ይመስላል? የዋሽንግተኑ ወኪላችን መክብብ ሸዋን በስልክ አነጋግሬው ነበር። መክብብ አሜሪካ ውስጥ ባነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን አስተያየት ይንደረደራል። 

መክብብ ሸዋ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ