የድርቅ ስጋት በአፍሪቃ ቀንድ
ዓርብ፣ መጋቢት 28 2004ማስታወቂያ
በዚህ ዓመት በአፍሪቃ ቀንድ መጣል የነበረበት የበልግ ዝናም ማነስ በአንዳንድ አካባቢም ጨርሶ መጥፋቱ አሳሳቢ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም ዓቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት በእንግሊዘኛው ምህፃር USAID አስታወቀ ። የድርጅቱ አስተዳዳሪ ዶከተር ራጂቭ ሻሃ ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የዝናሙ መጥፋት ባለፉት 2 ዓመታት በድርቅ በተጠቃው በአካባቢው ህዝብ ላይ ተጨማሪ እልቂት እንዳያስከትል ማስጋቱን ተናግረዋል ። ዶክተር ሻህ በአፍሪቃ ቀንድ የፖለቲካና የድርቅ ሁኔታ ላይ ከምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት በእንግሊዘኛው ምህፃር IGAD መሪዎች እና ከኢትዮጵያ ጠቅልይ ሚኒስተር አቶ መለስ ዜናዊ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ የአዲስ አበባው ወኪላችን ታደሠ እንግዳው ተከታትሎ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።
ታደሰ እንግዳው
ሂሩት መለሠ
ሸዋዮ ለገሠ