እ.አ.አ የካቲት አስራ ሶሶት ለየካቲት አስራ አራት አጥቢያ ይህች ከተማ በተደበደበች ወቅት በርካታ ህዝብ የተፈጀ ሲሆን ከተማይቱም እንዳልነበረች ሆናለች ። ድሬስደን በቦምብ የጋየችበት ይህ ለሊት በከተማይቱ ህዝብ ዘንድ በየዓመቱ ይታሰባል ። ይሁንና የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ በዚህ የመታሰቢያ ዕለት ወደ ከተማይቱ የሚመጡ ያልተጋበዙ ዕንግዶች የህዝቡን ስሜት እየረበሹ ነው ።