የዳርፉር የሰላም ዉልና ትርጓሜዉ
ሐሙስ፣ የካቲት 18 2002ማስታወቂያ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፥ የአረብ ሊግ፥ የአፍሪቃ ሕብረትን የመሳሰሉት ድርጅቶችና ብሪታንያና ፈረንሳይን የመሳሰሉ ምዕራባዉን ሐገራት የሱዳን መንግሥትና የፍትሕና የእኩልነት ንቅናቄ (JEM በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ) የተሰኘዉ አማፂ ቡድን ዶሐ ቀጠር ዉስጥ ለተፈረሙት ዉል ድጋፋቸዉን እየገለጡ ነዉ።የሥምምነቱ ጥሩነት ተነግሮ ሳያበቃ ግን ዳርፉር ዉስጥ የመንግሥት ጦርና ሸማቂዎች መጋጨታቸዉ ተዘግቧል። ሥምምነቱንና ተቢራዊነቱን በተመለከተ ነጋሽ መሐመድ የአፍሪቃ ቀንድ የፖለቲካ ጉዳይ አዋቂ ሮላንድ ማርሻል በስልክ አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ አጠናቅሮታል።
ነጋሽ መሀመድ
ሂሩት መለሰ